በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ ሦስት አዳዲስ አማንያን በበዓለ ጥምቀት ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አገኙ!

ኤክቱስ ጥር 13/2018 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ በዓላት ላይ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ ሦስት አዳዲስ አማንያን ተጠምቀው የሥላሴን አግኝተዋል።

በመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት 408፣ በይርጋጨፌ ወረዳ ቤተ ክህነት 524፣ በኮቾሬ ገደብና ጮርሶ ወረዳዎች ቤተ ክህነት 191፣ በቡሌና ረጴ ወረዳዎች ቤተ ክህነት 88፣ በኮሬ ወረዳ ቤተ ክህነት 301፣ በቡርጂ ወረዳ ቤተ ክህነት 171 አዳዲስ አማንያን ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አግኝተዋል።

ሀገረ ስብከቱ ኢ-አማንያንን ለማስጠመቅ በአከባቢው ቋንቋ የሚያስተምሩ ሰባኪያነ ወንጌል በመመደብ በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል።

Scroll to Top