በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

አንድ መቶ ሃያ አዳዲስ አማንያን በብፁዕ አቡነ ገሪማ ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አገኙ!

ኤክቱስ ጥር 11/2018 ዓ.ም

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት በዲላ ከተማ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል ዕለት አንድ መቶ ሃያ አዳዲስ አማንያን በብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አግኝተዋል።

በዕለቱ ከአንድ መቶ ሃያ ተጠማቂያን መካከል አንድ መቶ አስሩ ኢ-አማንያን ሲሆኑ አስሩ ደግሞ ሕጻናት መሆናቸው ተገልጿል።

Scroll to Top