በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በሀገረ ስብከቱ የሚሠሩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ!

ኤክቱስ ጥር 6/2018 ዓ.ም

ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት የሚሠሩ በርካታ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ሀገረ ስብከቱ በዲላ ከተማ የሚያስገነባው የመንበረ ጵጵስና ግንባታ፣ በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሚሠራው የውኃ እና የዶሮ ልማቶች ተጎብኝተዋል።

በተጨማሪም በአንዲዳ የሚገኘው የአዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት መደበኛ የመማር የማስተማር ሂደት፣ አዲስ ለመገንባት የታሰበበት ቦታ፣ የተማሪዎች የማደርያና የመመገቢያ ክፍላት እንዲሁም የአብነት ትምህርት ቤቱ ጽሕፈት ቤት ተጎብኝቷል።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ በአጠቃላይ ስለሚሠሩ የልማት ሥራዎች ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ብፁዕነታቸው በሀገረ ስብከቱ የተሠሩ ሥራዎችን እና ደቀ መዛሙርቱን በመጎብኘታቸው እና ቡራኬ በመስጠታቸው እጅግ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ሊቀ ጳጳስ በተመለከቱት ሥራዎች ፍጥነት መገረማቸውን የገለጹ ሲሆን ሁሉም አካል ከብፁዕነታቸው አጠገብ ከሆነ ከዚህ በላይ በርካታ ሥራዎችን በሀገረ ስብከታቸው እንደሚሠሩና ገና ብዙ ያልተጠቀምንባቸው አባት መሆናቸውን ገልጸው እግዚአብሔር ሀገረ ስብከቱን በፍጹም ሰላም እንዲጠብቅ በመማጸን ጉብኝታቸውን በጸሎት ፈጽመዋል።

በመርሃግብሩ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌን ጨምሮ የክፍል ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

Scroll to Top