በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ በክብር ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ እረፍት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ!!

ኤክቱስ ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በቀድሞ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት በነበሩት የክብር ዶክተር በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም ድካም በማረፋቸው ምክንያት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።

ብፁዕነታቸው በመልእክታቸው እንደሀገረ እንደርሳቸው ያለ አስታራቂ፣ የዋህ እና ደግ አረጋዊ አባት ማጣታችን ምን ያህል አሳዛኝ እንደሆነ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ለመላው የእስልምና እምነት ተከዮች፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለመላው ኢትዮጵያውያን ወዳጆቻቸው መጽናናትን ይላክልን ብለዋል።

Scroll to Top