በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

November 2024

ክርስቲያናዊ ህይወት

ክርስትና የሚለው ቃል “XPIETIAVOS” ኽርስቲያኖስ ከሚለው የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም የክርስቶስ መሆን ማለት ነው፡፡ ክርስትና ሰዎች በፍቅረ እግዚአብሔር ተስበው፤ ፈጣሪያቸውን አውቀው፤ እረፍትን ሽተው፤ በህጉና በትእዛዙ ፀንተው፤ ለመኖር ሲሉ ከዓለም ፈቃድ ተለይተው የሚኖሩበት ህይወት ነው፡፡ ይህንንም ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀመዝሙር ዮሐንስ “ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የስጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለገንዘብም መመካት ከዓለም ስለሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ÷ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም፡፡ ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ የእግዚያብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘለዐለም ይኖራል” (1ዮሐ 2፡16) በማለት ክርስቲያን ለመሆን በመጀመሪያ ዓለምን መካድ እንዳለብን ያስተምረናል፡፡ በክርስትና ወድቆ (ተረግሞ) የነበረው የሰው ዘር እንደ ተነሳ (እንደ ተፈታ)፤ የታመመው እንደ ተፈወሰ፤ የረከሰው እንደ ተቀደሰ፤ የሞተው እንደተነሳ፤የተሰበረው እንደተጠገነ፤ የሳተው እንደ ተመለሰ ይታመናል፡፡ የክርስትና መስራቹ ራሱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፡፡ “በዚህችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሰራለሁ፡፡ የገሀነም ደጆችም አይችሏት” (ማቴ 16፡18) በማለት ቤተክርስቲያን ሳይሆን ቤተክርስቲያኔን የራሱ እንደሆነች በህያው ቃሉ አረጋግጦልናል፡፡ ክርስቲያኖች ክርስቲያን ከመባላቸው አስቀድሞ ምዕመናን (መዝ 100፡7) ፤ ደቀመዛሙርት (ኢሳ 8፡16) ፤ ወንድሞች (ማቴ 8፡10) የመሳሰሉት በመባል ይጠሩ ነበር፤ ነገር ግን ደቀመዛሙርቱ ክርስቲያን ተብለው ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰየሙት በአንጾኪያ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት እንደነበር ቅዱስ መጽሀፍ ይነግረናል፡፡ (የሐዋ 11፡26) በምድራችን በሺዎች የሚቆጠሩ ሃይማኖቶች ይገኛሉ፡፡ የሃይማኖታቸውን መስራች ስናጠና ግን ሰዎች ሆነው እናገኛለን፡፡ ትምህርታቸው ዛሬም በተከታዮቻቸው ይኑር እንጂ እነርሱ ግን በህይወት የሉም፤ የክርስትና ዋና መስራች ግን ትናንት የነበረ ዛሬም ያለ ወደፊትም ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ዐልፋና ዖሜጋ ዘዓአለማዊ በመሆኑ ዛሬም ስራውን አላቆመም ማለት ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ህይወት ለመኖር ክርስቲያኖች የሚከተለውን መተግበር እንዳለብን የህይወት ምንጭ የሆነው መጽሀፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡ 1.    እግዚያብሔርን ማወቅ መቼም ዓለም አንድ መንደር በሆነችበት ዘመን ስለ እግዚያብሔር ያልሰማ አለ ብሎ ለመናገር ያስቸግራል፡፡ ይሁን እንጂ ከዕውቀት ብዛት እግዚአብሄርን የካዱ (እግዚአብሔር የለም) ያሉ በርካታ ሰዎች በምድራችን መኖራቸው ግልጽ ነው፡፡ ይህም ስንፍና እንጂ እውቀት እንዳልሆነ ልበ አምላከ ቅዱስ ዳዊት ይነግረናል፡፡ “ይበል አብድ በልቡ አልቦ እግዚአብሔር” ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል (መዝ 13፡1)፡፡ ፍልስፍና ማለት ጥበብን ማፍቀር ማለት እንጂ እግዚአብሄርን አለማወቅ ወይም መካድ ማለት አይደለም፡፡ አንድ ልጅ አባቱን አላውቅህም አባቴ አይደለህም ስላለው አባቱ አልወለደውም ማለት አይደለም እንዳውም ልጁ ሲጠራ አባቱን የካደ ልጅ ተብሎ ይጠራል፡፡ እግዚአብሄርን ማወቅ፡- ትርጉም ያለው ሕይወት ይሰጣል በምድራችን ትርጉም ያለው ሕይወት ማለት ምን አልባት የሚመስለን ሀብት፤ ንብረት፤ ስልጣን ፤ ጥሩ መልበስ፤ ጥሩ መመገብ ፤ ጥሩ ቤት መኖር ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን ትርጉም ያው ህይወት መኖር የሚቻለው እግዚአብሄርን ሲያውቅ ነው፡፡ በዚህ ዘኪዎስ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል፡፡ ዘኪዎስ ጌታውን ሳያውቅ የኖረበት ዘመን ትርጉም አልባ ህይወት ነበር አምላኩን ሲያውቅ ግን “ጌታ ሆይ ካለኝ ሁሉ እኩሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ ማንንም በሃሰት ከስሼ እንደሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ አለው” (ሉቃ 19 ፤9) በማለት አዲሱ ክርስቲያናዊ ህይወት ምን እንደሚመስል ነግሮናል፡፡ ታሪክን ይቀይራል ሰዎች እግዚአብሄሔርን ሲያውቁ ዘማዊ የነበረው ድንግል፤ ዘረኛና ወገንተኛ የነበረው ሁሉን በክርስቶስ አንድ አድርጎ የሚያይ ፍትሃዊ፤ አሳዳጅ የነበረው ስለ ክርስቶስ ተሳደጅ፤ ክፉ የነበረው ደግ፤ ዘፋኝ የነበረው ዘማሪ፤ ነፍሰ ገዳይ የነበረው የሰውን ህይወት የሚያድን ወዘተ ይሆናል፡፡ለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ ጥሩ አስረጅ ይሆናል፡፡ 2.    በዕምነት ማደግ ብዙዎች ክርስቲያን ተብለው ይጠራሉ ጥቂቶች ብቻ በእምነት ውስጥ በጥበብ ይኖራሉ፡፡ “ዕምነት ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነውና” (ዕብ11፡1) የሰው ልጅ በሃይማኖት ካልኖረ ለምኞቱ ገደብ የለውም፡፡ ያለኝ ይበቃኛል አይልም፡፡ አመንዝራ ሲያይ በፍትወት ስሜት ይቃጠላል፣ የወይን ጠጅ በብርሌ ባማረ መልኩ ባየ ጊዜ መጠጥ ያምረዋል ለዚህ እኮ ጥበበኛው ጠቢቡ ሰለሞን “ከተማን ከመግዛት ራስን መግዛት ይበልጣል ያለው” 3.    በእግዚአብሔር ፍቃድ መኖር እግዚአብሔር ከእኔ ይልቅ ስለ እኔ ያስባል ብሎ ማመን ነው፡፡የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ለዘለዓለም ይኖራል፡፡(የሐ2፡17) የጌታችንም ፈቃድ ሁሉ የእግዚአብሔር እንደሆነ ሲያስተምር “አባት ሆይ ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ ነገር ግን የእኔ ፍቃድ አይሁን የአንተ እንጂ”(ሉቃ22፡42) ምክንያቱም ሀዋርያው እንደተናገረው ”ስለ በጎ ፈቃድ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሰራ እግዚአብሔር ነውና” እንዲል (ፊሊ1፡13) 4.     እግዚአብሔርን መምሰል ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ዓለም ሶስት ዓመት ከሶስት ወራት በአገልግሎት ሲቆይ በርካታ ትምህርቶችን ከማስተማሩም በላይ በሕይወቱ አብነት ለመሆን መልካም ሥራ ካደረገ በኋላ ከመዝ ግበሩ  እናንተም እንዲሁ አድርጉ(ዮሐ13፡14)(ምንም እንኳን መልካምነት የባህርይው ቢሆንም) በማለት ክርስቲያኖች በሕይወት ዘመናቸው ክርስቶስን መምሰል እንዳለባቸው መጽሀፍ ይስተምረናል፡፡ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስም ይህንን ቃል ”እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ”(1ኛቆሮ 11፡1) በማለት ያረጋግጥልናል፡፡በመሆኑም የመንፈስን ፍሬ በማድረግ የስጋን ሥራ በመተው አምላካችንን መምሰል ይገባናል ማለት ነው፡፡(ገላ 5፡18)ይህንን በማድረግ ቅዱሳን ቅድስናን ገንዘብ አድርገዋል፡፡“እግዚአብሔር መምሰል ግን ለአሁኑ እና ለሚመጣው ተስፋ ስላለው ለነገር ሁሉ ይጠቅማል”(2ጢሞ 4፡8) 5.    ፍቅር ሊኖረን ይገባል በክርስትና መጀመሩያውም መጨረሻውም ፍቅር ነው፡፡ ምክንያቱም “ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፡፡እግዚአብሔር ፍቅር ነውና” (1ዮሐ 4፡8) በመሆኑም ያለ ፍቅር ክርስትና የለም፡፡ቢኖር እንኳን ቅ/ጳውሎስ እንደተናገረው ከንቱ ነው “ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ”(1ቆሮ 13፡1) 6.    ከመስቀሉ መካፈል የጠፋውን በግ ፍልጋ ራሱን ባዶ ያደረገው ክርስቶስ (ፊሊ 2፡8) ድሉ በመስቀል ስለ ተጠናቀቀ ክርስቲያኖች በሕይወት ዘመናቸው ከመስቀሉ ተካፋይ መሆን አለባቸው፡፡ ለዚህም ከመስቀሉ ስር የተሰጠችንን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን መውሰድ፤ የተቆረሰውን ቅዱስ ስጋ መብላት፤ የፈሰሰውን ክቡር ደም መጠጣት ይኖርብናል ማለት ነው፡፡ (ዮሐ 19፡27፤ ዮሐ 6፤56) ይህ ሁሉ ሲሆን ለዘለዓለም በሕይወት እንኖራለን ማለት ነው፡፡ ስብሃት ለእግዚያብሔርወለወላዲቱ ድንግልወለ መስቀሉ ክቡርአሜን

ክርስቲያናዊ ህይወት Read More »

ትምህርተ ሃይማኖት

በሊቀ ካህናት ኃይለሥላሴ ዓለማየሁ ወልድ ዋሕድ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና የሌሎች አኃት አብያተ ክርስቲያናት መሠረታዊ እምነት «ተዋሕዶ» ነው። ተዋሕዶን የሚተረጉም ኃይለ ቃልም ፣ «ወልድ ዋሕድ» የሚለው ነው። ወልድ ዋሕድ ለሚለው ሥያሜ መሠረቱ «ቃል ሥጋ ኮነ» የሚለው ቃለ ወንጌል ነው። ዮሐ ፩፥፲፬። ስለሆነም፣ የዚህ ዝግጅት ዐቢይ ርእስ /ዋና ርእስ/ ወልድ ዋሕድ እንዲባል ተመርጦአል።በዚህ ዝግጅት የሚቀርቡ ንኡሳን አርእስተ ትምህርት በየርእሳቸው እየታተቱ የሚቀርቡ ሆኖ ጥናቱ በማስረጃ የተደገፈ እንዲሆን ለማድረግ አዘጋጁ ተገቢውን ጥረት ያደርጋል። ለወጣቱ ግንዛቤ ይሰጣል ተብሎ የሚታመንበት ዝግጅት እንዲሆንም በቀላል አገላለጽ ለማቅረብ ይሞክራል። የትምህርተ ሃይማኖት ምሥጢራዊ ይዘት ከመጽሐፍ ቅዱስና ከአበው ሊቃውንት የትርጉም ዘይቤ እየተገናዘበ ይቀርባል። የዝግጁቱ ዋና ዓላማ፣ ወጣቶች የትምህርተ ሃይማኖት ግንዛቤያቸውን እንዲያሰፉ ማድርግ በመሆኑ፣ የቤተክርስቲያናችንን መሠረተ እምነት ሊያዛቡ ከሚችሉ አዳዲስ አስተሳሰቦችና የግል አስተያየቶች ፍጹም ነፃ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ሆኖ እንዲቀርብ ተገቢው ጥንቃቄ ይደረጋል። ከአንባቢያን ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ሁሉ አስፈላጊው ትኩረት እየተሰጣቸው ተገቢውን መልስ እንዲያገኙ ማድረግ የአዘጋጁ ተቀዳሚ ተግባርና ግዴታ ነው። ይህን ዝግጅት የሚከታተሉ አንባብያንም እያንዳንዱን ኃይለ ቃል፣ በማስተዋል መከታተል፣ ምሥጢሩንና ቁም ነገሩንም በጥንቃቄ መቅሰም ይጠበቅባቸዋል። ጥበብና ማስተዋል የሚገኘው ከእግዚአብሔር ነውና እግዚአብሔር ጥበቡንና ማስተዋሉን ይስጠን። ከእግዚአብሔር አጋዥነትና ረድኤት ውጪ ምንም ምን የሚሆን ነገር ስለሌለ፣ በተለይም ባሕረ ጥበባት የሆነውን ትምህርተ መለኮት ለማቅረብ መሞከር፣ ውቅያኖስን በእንቊላል ቅርፊት… ማለት በመሆኑ፣ የጥበባት አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ጥበቡንና ማስተዋሉን እንዲሰጠን እንለምነዋለን። ትምህርተ ሃይማኖት መለኮታዊ ምሥጢርን የሚያስረዳ እንደመሆኑ ትምህርቱ ጥልቅ፣ ረቂቅና ምጡቅ ነው። ይሁንና በዚህ ዝግጅት ግን እንደ ትምህርቱ ጥልቀትና ምጥቀት ሳይሆን፣ እንደ አዘጋጁ የዕውቀት ውሱንነትና እንደ ተቀባዩ የአእምሮ ስፋት መጠን፣ ግልጽ በሆነ አቀራረብ ባጭር ባጭሩ ይቀርባል። የሃይማኖት ትርጉም  ሃይማኖት ምንድን ነው? ሃይማኖት ወይም እምነት ማለት ማመን፤ መታመን፤ የፈጣሪን ሕልውና ማወቅ፤ ከሃሊነቱን፣ መግቦቱንና ቸርነቱን መረዳት፤ መለኮታዊ እውነታዎችን በትክክል መቀበል፤ በእግዚአብሔር መለኮታዊ ሥራ ፈጽሞ አለመጠራጠር፤ ጥርጥርን ከኅሊና ማስወገድ፤ ስለ ሰማያዊ ሕይወት ጽኑ ተስፋ ማድረግ በሚሉ አገላለጾች ይተረጐማል። ሃይማኖት በረቂቅ ሐሳብ፣ በልብ ሰሌዳነት፣ የሚጻፍ የአእምሮ መጽሔት ነው። ሃይማኖት የኅሊና መሰላል በመሆኑ የዓለምን አስቸጋሪ ዳገት ይወጡበታል። ሃይማኖት የሕይወት መርከብ በመሆኑ ገፊውን ማዕበል ተቋቁመው ባሕሩን ይሻገሩበታል። ንጉሠ ሰማይ ወምድር እግዚአብሔርን ደስ ያሰኙበታል። ዕብ ፲፩፥፮። ልክና መጠን፣ ወሰንና ዳርቻ የሌለው መለኮታዊ ባሕርይ የሚታየው፣ ሕልውናው ከሃሊነቱና መግቦቱ የሚታወቀው በሃይማኖት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ የሃይማኖትን ኃይል ሲተረጉም፦ «እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፣ የማናየውን ነገር የሚያስረዳ ነው።» ይልና በመቀጠልም «ነአምር ከመ ተፈጥረ ዓለም በቃለ እግዚአብሔር። ዓለም በእግዚአብሔር ቃል እንደተፈጠረ እናውቃለን።» ብሎአል። ዕብ ፲፩፥፩-፫። ሃይማኖት ፍጡርን ከፈጣሪው ጋር የሚያገናኝ የኅሊና መሰላል በመሆኑ ፍጡር የሃይማኖት መሰላሉና ድልድዩ ከተሰበረበት ወደ ፈጣሪው መድረስ ይሳነዋል፤ ሌላ መድረሻ ሌላ መንገድ ፈጽሞ የለውም። የሃይማኖት ኃይል ልዩና ዕፁብ ድንቅ የሚያሰኘው፣ ምድራዊ ባለሥልጣን የማይገዛውን የሚገዛ፣ በዓይነ ሥጋ የማይታየውን የሚያሳይ፣ በእጅ የማይዳሰሰውን የሚዳስስ፣ በሥጋዊ ጥበብ የማይመረመረውን የሚመረምር ምሥጢር መሆኑ ነው። ማቴ ፲፮፥፲፯። ልዕልና ነፍስ /የነፍስ ልዕልና/ ክብረ ነፍስ የሚገኘው በሃይማኖት ነው፤ ከሃይማኖት ውጪ የሚሆነው ሁሉ ኃጢአትና በደል ነው። «ወኲሉ ዘይከውን ዘእንበለ አሚን ኃጢአት ወጌጋይ ውእቱ። በእምነት ያልሆነ ሁሉ ኃጢአትም፣ በደልም ነው።» ሮሜ ፲፬፥፳፫። የሚታይና የማይታይ፣ ግዙፍና ረቂቅ፣ ሁሉ ከማይታይ እንደሆነ ማለትም በመለኮታዊ ሥልጣን የተገኘ መሆኑን ያሳውቃል። እግዚአብሔር ለፍጥረቱ ሁሉ መገኘት ምክንያት ሳይሻለት በከሃሊነቱ እምሀበአልቦ ፈጥሮታል። ይህን ማወቅ የሚያስችል ከሃይማኖት ውጪ ሌላ ጥበብ ፈጽሞ የለም። የሰው ልጅ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወራሽ የመሆን ዕድል የሚያገኘው በሃይማኖት ብቻ ነው። በዓለም ያለውን ሥርዓት በቀላሉ በምሳሌነት ማየት ይቻላል፤ ይኸውም የአንድን ሰው ሃብትና ንብረት ለመውረስ በቀላሉ ባለመብት መሆን የሚቻለው የባለጸጋው ወይም የባለሀብቱ ልጅ ሆኖ መገኘት ሲቻል ነው። በእግዚአብሔር መንግሥትም በሃይማኖት ልጅነትን ካላገኙ የመንግሥቱ ወራሽ መሆን አይቻልም። «እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።» እንዳለ ጌታ በቅዱስ ወንጌል። ዮሐ ፫፥፭። «… ስለዚህ ከእንግዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም። ልጅም ከሆንክ ደግሞ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።» ገላ ፬፥፬-፯።ሃይማኖት በአማኙ ዘንድ ሦስት ነገሮች ተሟልተው እንዲገኙ ግድ ይላል። እነዚህም፦ ፩. ትክክለኛ አረዳድ /እውነት/፪. የልብ ንጽሕና /ቅንነት/፫. መጥዎተ ርእስ፣ ማለትም ጥብዓት፣ ራስን መካድ፣ ራስን አሳልፎ ለሃይማኖት መገዛት ፈቃደ ሥጋን አሸንፎ መስቀልን መሸከም የሚሉ ናቸው። እነዚህ መሠረታዊ ነገሮች ያልተሟሉለት አማኝ ግብዝ ሃይማኖተኛ ይባላል። ማስረጃ «… እግዚአብሔር አንድ እንደሆነ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ። አጋንንት ደግሞ ያምናሉ፤ ይንቀጠቀጡማል። …» ያዕ ፪፥፲፬-፳፪። ማር ፭፥፯። ጌታም በቅዱስ ወንጌል እንዲህ ይለናል። «በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።» ማቴ ፯፥፳፩። «ሕዝቡንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጠርቶ፣ እንዲህ አላቸው፤ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፣ ራሱን ይካድ። መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።» ማር ፰፥፴፬። ሉቃ ፱፥፳፫። ማቴ ፲፥፴፰፣ ፲፮፥፳፬። «ወኅሊናሁሰ ለነፍስትነ ሞተ ያመጽእ ላእሌነ፤ ወሕሊናሁሰ ለመንፈስ ሰላመ ወሕይወተ ይሁብነ። የሥጋችን ፈቃድ ሞትን ያመጣብናል /ያስፈርድብናል/ የነፍሳችን ፈቃዱ ግን ሰላምን ከእግዚአብሔር ጋር አንድነትን ድኅነትን ይሰጠናል። እስመ ኅሊናሁ ለነፍስትነ ፀሩ ለእግዚአብሔር ውእቱ። የሥጋችን ፈቃዱ የእግዚአብሔር ጠላቱ ነውና ሞትን ያመጣብናል።» ሮሜ ፰፥፭-፰።የሃይማኖት ዓላማውና ግቡ፣ ሀልዎተ እግዚአብሔርን ማሳወቅና ፍጡር በፈጣሪው ሕግና ትእዛዝ እየተመራ ዘለዓለማዊ ክብር እንዲያገኝ ማድረግ ነው። ማቴ ፳፭፥፴፬። ሀልዎተ እግዚአብሔርን ማወቅ ማለትም ቅድመ ዓለም የነበረ፣ በማዕከለ ዓለም ያለ፣ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር፣ ፈጣሪ፣ መጋቢ ሠራዒ፣ በመለኮታዊ ባሕርዩ ጸንቶ የሚኖር፣ ለመንግሥቱ ሽረት፣ ለሕልውናው ኅልፈት የሌለበት አንድ ፈጣሪ፣ አንድ አምላክ መኖሩን አውቆ ማመን ማለት ነው። «እስራኤል ሆይ ስማ፤ አምላክህ እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው።» ዘዳ ፭፥፬። የማይታይና የማይመረመር፣ የማይገሰስና የማይዳሰስ፣ ሕያወ ባሕርይ እግዚአብሔር በከሃሊነቱ ሁሉን የፈጠረ፣ በመግቦቱ ሁሉን የሚያስተዳድር፣ በቸርነቱ ሁሉን የሚጠብቅ አምላክ በመሆኑ ለፍጥረቱ የሚታወቅበት ገጽታ አንዱ ይኸው ነው። ሁሉን የሚገዛ፣ ሁሉን የሚያስተዳድር በመሆኑ ይቅርታውና መግቦቱ በሁሉም ላይ ነው። «እስመ ቅንየትከ ወምልክናከ ላዕለ ኲሉ፣ ይሬስየከ ትሣሃል ላዕለ ኲሉ። ማለት በሁሉ ላይ ያለ ሥልጣንህና አገዛዝህ ሁሉን ይቅር እንድትል ያደርግሃል።» እንዲል። «… እርሱ በክፉዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።» ማቴ ፭፥፵፭። በከሃሊነቱ ዓለምን የፈጠረ እግዚአብሔር የማይታይ፣ የማይመረመርና የማይዳሰስ፣ እንደሆነ ቢታወቅም፣ ባሕርዩ ከሚገለጽባቸው አያሌ መገለጫዎች ጥቂቶቹን በምሳሌነት መመልከት ይቻላል። እነሱም፦ ፩. ፈጣሪ፪. ከሃሊ፫. ምሉእ፬. ዘለዓለማዊ፭. ቅዱስ፮. ፍጹም፯. ማእምር /አዋቂ/ ጥበበኛ የሚሉ ናቸው። እነዚህን በዝርዝር እንመለከታለን። እግዚአብሔር ፈጣሪ ነው ፈጣሪ ስንል የሌለን ወይም ያልነበረን ነገር በሥልጣኑና በከሃሊነቱ ያስገኘ፣ ዓለምን እምሀበአልቦ /ካለመኖር ወደ መኖር/ የፈጠረ ማለታችን ነው። ዓለምን እምሀበአልቦ ያስገኘ፣ በመለኮታዊ  ሥልጣኑ የሚታየውንና የማይታየውን፣ ግዙፉንና ረቂቁን ፍጥረት ሁሉ የፈጠረ እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር ዓለምን /ፍጥረቱን/ ለመፍጠር ምክንያት የሆነው መለኮታዊ ሥልጣኑ ብቻ ነው፤ የፍጥረታት ሁሉ አስገኝ እግዚአብሔር በመሆኑም የፍጥረታት ሁሉ ጌታና ባለቤት እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር ዓለምን ፈጥሮ እንዲሁ አልተወውም፤ በመግቦቱ ይጠብቀዋል፤ ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ እግዚአብሔር ብቻ በመሆኑና በመለኮታዊ ሥልጣኑ መሳይ ተወዳዳሪ ስለሌለውም እግዚአብሔር አንድ አምላክ ይባላል። እግዚአብሔር ዓለሙን ሲፈጥር፣ ይሁን ብሎ በቃሉ፣ በመለኮታዊ ሥልጣኑና በከሃሊነቱ ፈጠረው እንጂ ፍጥረታትን ለማስገኘት ሌላ አፍአዊ ምክንያት አላስፈለገውም። እንደዚህ ያለ መለኮታዊ ሥልጣን በሰማይም በምድርም ስለሌለ፣ እግዚአብሔር ብቻ ፈጣሪ እንዲባል ያደርገዋል። «ዓይናችሁን ወደ ላይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ እነዚህን የፈጠረ ማን ነው? ሠራዊታቸውን በቊጥር የሚያወጣ እርሱ ነው። ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል። በኃይሉ ብዛትና በከሃሊነቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም።» ይላል የእግዚአብሔር ቃል። ኢሳ ፵፥፳፮። በእግዚአብሔር ረቂቅ ሥልጣንና ከሃሊነት የተፈጠረ ፍጥረት ሁሉ ሥርዓት ተሠርቶለት፤ ወሰን ተበጅቶለት ይኖራል። ከተሠራለት ሥርዓት አይወጣም፤ ከተደነገገለት ወሰን አያልፍም። ለይኩን

ትምህርተ ሃይማኖት Read More »

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ምንድን ነው?

፩. ሥርዓት ቤተ ክርስቲያን  ምንድን ነው? ሥርዓት “ሠርዐ” ሠራ ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ደንብ፣ አሠራር፣ መርሐ ግብር ማለት ነው። ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ስንልም የቤተ ክርስቲያን ዕቅድ፣ የቤተ ክርስቲያን አሠራር መርሐ ግብር ወይንም ደንብ ማለታችን ነው። ሥርዓት የሚከተሉት ጥቅሞች አሉት፦ ሥራን ወጥ በሆነ መልኩ ለመፈጸም ማንኛውንም ነገር ወጥና ዘላቂ በሆነ መልኩ ለመሥራት ከየት ተጀምሮ በየት በኩል ሄዶ በየት በኩል እንደሚጠናቀቅ ወጥ የሆነ የአሠራር ሥርዓት ይዘጋጅለታል። የአንድ ሥራ አሠራር በትክክል ካልተነደፈና አካሄዱ ካልተስተካከለ፤ ሥራው የተዘበራረቀ ይሆናል ፍጻሜውም አያምርም።ማኅበረ ምዕመናንም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደጻፈው የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ አንድ ዓይነት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ያስፈልገናል። ብዙ ስንሆን አንድ ልቡና አንድ ሃሳብ የሚያደርገን ሥርዓት ነውና። /ኤፌ. ፬፥፫፤ የሐዋ. ፬፥፴፪፤ ሮሜ. ፲፭፥፮ የሃይማኖትን ምሥጢራት ለመጠበቅ ሥርዓት የሃይማኖት መገለጫ ነው። ጥምቀት፣ ቁርባን፣ ጾም፣ ጸሎት፣ ሥግደት፣ ወዘተ በማመን ብቻ የሚያበቁ ሳይሆን የአፈጻጸምና አተገባበር መንገድ /ሥርዓት/ ያስፈልጋቸዋል። የእነዚህ ሁሉ ዝርዝር አፈጻጸም በሥርዓት ውስጥ ይካተታል። ስለዚህ በአንዲት ርትዕትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን እምነት ሥር ያሉ ሁሉ ያቺን አንዲት እምነት የሚገልጹት አንድ ዓይነት በሆነ ሥርዓት ነው። ሥርዓት በመሠረተ እምነት /ዶግማ/ የምናምናቸውን በተግባር የምንገልጽበትና ተግባራዊ የምናደርግበት መንገድ ስለሆነ ሥርዓቱ ሲሠራና ሲፈጸም ሃይማኖታዊ አንድምታና ነጸብራቅ ይኖረዋል። ፪. ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ማለት ሕንፃው፣ የክርስቲያኖች አንድነት /ጉባኤ/ እና የምዕመኑ ሰውነት በመሆኑ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የምንለውም በእነዚህ በሦስቱ ላይ የተሠራውን ሥርዓት ነው። አንዳንዶቻችን ቤተ ክርስቲያንን ከራሳችን አርቀን ሌላ አካል አድርገን ስለምንመለከት ሥርዓቱ እኛን የሚመለከት አይመስለንም። ሥርዓቱ ግን የተሠራው ለሦስቱም የቤተ ክርስቲያን ትርጓሜዎች መሆኑን ማወቅ ተገቢ ነው። ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ምንጩ ወይንም መሠረቱ መጽሐፍ ቅዱስ፣ የቅዱሳን አባቶቻችን ጉባኤያት ውሳኔ /ሲኖዶስ/ እና አባቶቻችን ሊቃውንት በተለያዩ ጊዜ ያደረጓቸው ጉባኤያት ውሳኔዎች ናቸው። ሰንበትን ማክበር፣ በጻድቃን ስም አብያተ ክርስቲያናትን ማነጽ፣ የቁርባን ሥርዓት፣ የመሳሰሉት ከመጽሕፍ ቅዱስ የተገኙ ሥርዓቶች ናቸው። /ዘፍ. ፳፰፥፳-፳፪፤ ዘጸ. ፲፮፥፳፱፤ የሐዋ. ፩፥፲፪/።ወደ ቤተ ክርስቲያን የገባውንና የተቀደሰውን ንዋየ ቅድሳት እንደገና ወደውጭ አውጥቶ ለሥጋዊ ጥቅም ማዋል እንደማይገባ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፩ ረስጣ ፳፰/፣ ጥምቀት በፈሳሽ ውኃ መፈጸም እንዳለበት፣ ወንዶች ሴቶችን ሴቶች ደግሞ ወንዶችን ክርስትና እንዳያነሱ፣ ሥጋ ወደሙ ለመቀበል ፲፰ ሰዓት መጾም እንደሚገባ፣ ሥጋ ወደሙ በምድር ላይ እንዳይወድቅ /እንዳይነጥብ/፣ ያላመኑ ሰዎች ሥጋ ወደሙን መቀበል እንደሌለባቸው፣ ወዘተ ያሉት ደግሞ በሲኖዶስ /የቅዱሳን አባቶቻችን ጉባኤያት/ የተገኙ ሥርዓቶች ናቸው።ከእናቱ፣ ከእህቱ፣ ከአክስቱ ወይንም እንደዚህ ባለ ሁኔታ ከምትታሰብ ሴት ጋር ካልሆነ በቀር አንድ ኤጲስ ቆጶስ፣ አንድ ቄስ፣ አንድ ዲያቆን፣ ወይንም ሌላ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ከማንኛውም ሴት ጋር አብሮ እንዳይኖር፤ ስለ መናፍቃን ጥምቀት፣ ስለ ትንሣኤ በዓል አከባበር፣ ስለ ድንግልና ኑሮ፣ ወዘተ ደግሞ በተለያዩ ጉባኤያት አባቶቻችን ያስተላለፏቸው ውሳኔዎችና ቀኖናዎች የተገኙ ሥርዓቶች ናቸው። የቤተ ክርስቲያን አመሰራረትና የቅዳሴ አገልግሎት ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንጻር መቼም በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን እየሰፋች ከሀገር ቤት አልፋ በውጭ ሀገርም አብያተ ክርስቲያናት እየታነጹ ስለሆነና ሁላችንም የቻልን ዘወትር ቅዳሴ በሚቀደስባቸው ዕለታት፣ ያልቻልን ደግሞ በዕለተ ሰንበት ለቅዳሴ ወደ ቤተ ክርስቲያን ስለምንሄድ ስለ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን አመሠራረት፣ አሠራርና ቡራኬ፣ እንዲሁም ስለ ሥርዓተ ቅዳሴ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንጻር እንዴት መሆን እንዳለበት እንገነዘባለን። ለዚህም እንዲረዳን እንደሚከተለው እናያለን። ቤተ ክርስቲያን ሲሠራ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን መሠረተ ቃሉ ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል /ቤቴሰ ቤተጸሎት ትሰመይ/ የሚለው /ኢሳ. ፶፮፥፮-፯፤ ኤር. ፯፥፲፩፤ ማቴ. ፳፩፥፲፫፤ ማር.  ፲፩፥፲፯፤ ሉቃ. ፲፱፥፵፮፤ ዮሐ. ፪፥፲፮-፲፯/ ሲሆን ቤተ ክርስቲያን የዋዛ የፈዛዛ፣ የሳቅ የስላቅ፣ የጨዋታ፣ የመብል፣ የመጠጥ ቤት ሳትሆን፤ ምዕመናን ኃጢአት ቢሠሩ ሰለ ኃጢአታቸው የሚያዝኑባት የሚያለቅሱባት ንጹሕ የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ካህናት የሚያስተምሩባት፣ ምዕመናን የሚማሩባት የግል ጸሎት፣ የማኅበር ጸሎት የሚጸልዩባት፣ በኅብረት የሚያስቀድሱባት ሥጋ  ወደሙ የሚቀበሉባት፣ የኃጢአት ሥርየት የሚያገኙባት፣ ሕፃናት በአርባ ቀንና በሰማንያ ቀን በጥምቀተ ክርስትና አማካኝነት ከሥላሴ የጸጋ ልጅነት የሚቀበሉባት፣ ኢአማንያን የነበሩ በመምህራን ትምህርት አምነው ክርስቲያን የሚሆኑባት፣ ለክህነትም ሆነ ለአባልነት የዘር ሐረግ የማይቆጠርባት ዓለም አቀፋዊት የእግዚአብሔር ቤት ናት፡፡ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ስትመሠረት ጀምሮ ሥርዓት አላት። የምትመሠረተው ባንድ ግለሰብ ስም ሳይሆን በካህናትና በምዕመናን ጥያቄ በሀገረ ስብከቱ ኤጲስ ቆጶስ ፈቃድና ትእዛዝ ነው፤ ካለኤጲስ ቆጶስ ፈቃድ ከመጽሐፉ ትዕዛዝ ወጥቶ አንዱ ቢያቋቁም ወይም ቢሠራ ቤተ ክርስቲያን ናት ብለው ለዘለዓለሙ በዛች ቤተ ክርስቲያን አይቁረቡባት፤ እንደገበያ፣ እንደእንስሳት በረት ፈት ሆና ትኑር ይላል። /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፩-፫/። ቤተክርስቲያን ለመሥራት ፈቃድ ከተገኘ በኋላ ስለ አሠራሯ የሚከተለው ሥርዓት ተሠርቶላታል። ቤተ ክርስቲያኗ ስትሠራ ደጆችና መስኮቶች አውጡላት ዛፍ ቅረጹላት ሐረግ ሳቡላት እንደሚል በተቻለ መጠን ሊያስጌጧት ይገባል የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ናትና።  በሰማይ ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት እንዲያበሩ፣ ሰባቱ ሰማያት ብሩሃን እንዲሆኑ ቤተ ክርስቲያንም ብርህት ትሁን፤ ይልቁንም ክቡራት መጻሕፍት ሐዲሳት፣ የጳውሎስ መልእክታት፣ የሐዋርያት መልእክታት፣ ግብረ ሐዋርያት በሚነበቡበት ጊዜ የበራች ትሁን፣ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ ያለውም ይህንኑ ያመለክታል። /ማቴ. ፭፥፲፬/። ቅዱስ ወንጌል በሚነበብበት ጊዜ ግን ፈጽማ የበራች ትሁን፤ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ ያለው ይሻል። /ዮሐ. ፱፥፭/። ቤተ ክርስቲያን ሲባረክ ቤተ ክርስቲያን ሕንፃዋ ተፈጽሞ በምትባረክበትና በምትቀደስበት ጊዜ ከኤጲስ ቆጶሱ ጋር ሰባት ቀሳውስት አብረውት ሊኖሩ ይገባል፣ ታቦቱም በሚባረክበት እንደዚሁ ሊሆን ይገባል፣ ኤጲስ ቆጶሱ እግዚአብሔር ሰውን የሚያከብርበት ራሱን የሚያስመስልበት ነውና ደስ በሚያሰኝ በቅብዐ ቅዱስ በሜሮን ያክብራት ያትማት፣ ታቦቱንም በመቅደስ ውስጥ በመንበር ያስቀምጡባት ከታቦቱ ጋራ የዮሐንስን ወንጌል ያኑሩ ከደቀ መዛሙርቱም በጌታ ኢየሱስ አጠገብ የሚቀመጥ ጌታ የሚወደው ቅዱስ ዮሐንስን ነበርና። /ዮሐ. ፲፫፥፳፫/ ። ታቦቱም ሲቀረጽ ከላይ አልፋ፣ ቤጣ፣ የውጣ፣ ወኦ/ወዖ/ ይቀረጻል። ቀጥሎ እመቤታችንን፣ ከእመቤታችን ቀጥሎ ዮሐንስን፣ ቀጥሎ ቤተ ክርስቲያኑ የሚተከለው ታቦት መልአክም ቢሆን፣ ሰማዕትም ቢሆን፣ ጻድቅም ቢሆን ይቀረጻል። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ካልተሟሉ ታቦቱን ሊቀድሱበት አይገባም። ከቤተ ክርስቲያን የገባ ዕቃ የወርቅ፣ የብር፣ ፃሕል ጽዋእ እርፈ መስቀል ቢሆን ንዋየ ቅድሳት ነው ተብሎ አቡነ ዘበሰማያት ከተደገመበት በኋላ ከቤታቸው ወስደው በፃሕሉ ፈትፍተው ሊበሉበት በጽዋው ቀድተው ሊጠጡበት አይገባም። ደፍረው ቢያደርጉ ሥርዓት ማፍረስ ነውና ይህን ያደረገ ቢኖር በአንድ ሁለት ተቀጥቶ ንሰሐውን እሰኪፈጽም ከምዕመናን ይለይ። /ዳን. ፭፥፩-፴፩/። በቤተ ክርስቲያንም ኤጲስ ቆጶሳት፣ ካህናት፣ ዲያቆናትና ምዕመናን እንዴት መቆም እንዳለባቸው ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚከተለው ይገልጻል። ኤጲስ ቆጶሳት የቤተ ክርስቲያን አዛዚያን እንደመሆናቸው በታቦቱ ፊት ይቁሙ፣ ቀሳውስትም መምህራን እንደመሆናቸው ከኤጲስ ቆጶሳት ቀጥለው ይቁሙ፣ ሊቀ ዲያቆናትም ከኤጲስ ቆጶስ አጠገብ ይቁሙ፣ ዲያቆናትም አገልጋዮች እንደመሆናቸው ከቀሳውስት ቀጥለው ይቁሙ፣ ከዲያቆናት ቀጥለው ሕዝቡ ሁሉ ባንድ ቦታ ይቁሙ፣ የሚበቃ ቦታ ቢኖር ሕፃናት በአንድ ወገን ለብቻቸው ይቁሙ፣ የሚበቃ ቦታ ከሌለ ግን ከአባቶቻቸው ጋራ ተስገው ይቁሙ፣ እንደዚሁም ሴቶች ባንድ ወገን /ቦታ/ ለብቻቸው ይቁሙ፣ ቦታ ቢገኝ ሕፃናት ሴቶች ባንድ ወገን ለብቻቸው ይቁሙ፣ ቦታ ባይኖር ግን ሕፃናቱ በፊት እናቶች በኋላ ይቁሙ፣ ደናግላን ሴቶችና ባልቴቶች ግን ከሴቶች በላይ ይቀመጡ ። /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፪ ድስቅ ፲፪ ኒቅያ ፷፩/። ሥርዓተ ቅዳሴ በቅዳሴ ጊዜ ስለሚደረጉና ሰለማይደረጉ ነገሮች ደግሞ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚከተለው ያዝዛል፦ በቅዳሴ ጊዜ የሚስቅ ሰው ቅዱስ ባስልዮስ በጻፈው በ፸፪ኛው አንቀጽ ካህን ቢሆን የሚያቀብል ነውና ሥጋ ወደሙን ከተቀበለና ካቀበለ በኋላ ወጥቶ አንድ ሱባዔ ይቀጣ ይጹም ይስገድ፣ የሳቀው ሕዝባዊ ቢሆን ግን ሥጋ ወደሙን ሳይቀበል ያን ጊዜ ፈጥኖ ይውጣ ይላል። ምነው ፍርድ አበላለጠ ካህኑን ተቀብሎ ወጥቶ ይቀጣ አለ፤ ሕዝባዊውን ሳይቀበል ወጥቶ ይሂድ አለ ቢሉ ካህኑ የሚቆመው ከውስጥ ነው ሲስቅ የሚያየው የለም። ካህኑ በቅዳሴ ጊዜ ቅዳሴውን ጥሎ ወጥቶ ሲሄድ ባዩት ጊዜ ቄስ እገሌ አባ እገሌ በመሥዋዕቱ ምን አይተውበታል ብለው መሥዋዕቱን ሳይቀር ይጠራጠሩታል፤ ስለዚህ ነው። ምዕመኑ ግን

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ምንድን ነው? Read More »

Scroll to Top