ኤክቱስ ኅዳር 17/2019 ዓ.ም
ላለፉት ዕለታት በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት የመስክ መቃኛ ሰነድ መሠረት የልማት እንቅስቃሴዎች በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል መሪነት ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል።
በዛሬው ዕለት በሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ በመልአከ ብርሃን አጥናፉ ማሞ እና በሀገረ ስብከቱ ቁጥጥርና የምግባረ ሰናይ ክፍል ኃላፊ በመምህር በየነ ክፍሌ በአራተኛው ቀን በዲላ ዳግማዊት ጌቴሴማኒ በአታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል።
ኃላፊዎቹ በቆይታቸው የገቢና ወጪ ሥርዓትን፣ የንብረት አያያዝን እንዲሁም የአጥር ግንባታ፣ አዲስ የተተከለ የቡና ችግኝ፣ የሸንኮራ አገዳ፣ የዘመናዊውን ትምህርት ቤት፣ ማስፋፍያ ክፍሎች፣ የአብነት ተማሪዎችን፣ለዓሣ ዕርባታ የታቀደውን ቦታ፣ ዘመናዊ የንብ ቀፎ እና የደብሩን ጠቅላላ ይዞታ ተመልክተዋል።
ይህ ጉብኝት የልማት ተግባራትን ለማጠናከር፣ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመለየትና የቀጣይ የሥራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

