በጌዴኦ ኮሬና እና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በዲላ እና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት ስር በሚገኘው በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሲከናወን የቆየው የዘመናዊ ዶሮ እርባታ ፕሮጀክት፤ አሁን ላይ ውጤቱን ለምዕመናንና ለአካባቢው ነዋሪዎች ማቅረቡን በደስታ ይገልጻል።
ይህ የልማት ስራ ሀገረ ስብከቱ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን በልማት ራሷን ለማስቻልና ማኅበረሰቡን ለማገልገል በጀመረው እንቅስቃሴ መሠረት፤ ዓለም አቀፉ የእንስሳት ምርምር ተቋም “International Livestock Research Institute (ILRI)” ከላዕከ ወንጌል ያሬድ አደመ ጋር በጋራ በመሆን የተከናወነ ሲሆን ጥራት ያላቸውና ለጤና ተስማሚ የሆኑ የሥጋ ዶሮዎችን ለሽያጭ አቅርቧል።
ምርቶቻችን በዘመናዊ መልክና በከፍተኛ እንክብካቤ ያደጉ፣ እንዲሁም በቀጥታ ከእርባታ ጣቢያው ለተጠቃሚ የሚቀርቡ በመሆናቸው በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲጠቀሙ ተጋብዘዋል።
📍 የሽያጭ ቦታ፦ ዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የዶሮ እርባታ ሥፍራ
⏰ የሽያጭ ቀንና ሰዓት፦ ከየካቲት 1 – 8 ቀን 2018 ዓ.ም (ዘወትር በሥራ ሰዓት)
“በኃይልህ ሰላም ፥ በጌጠኛ ቤትህም ልማት ይሁን” (መዝ 122፥7)
