ኤክቱስ ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም
በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት የሕግ ክፍል ዐቢይ ኮሚቴ መቋቋሙን ተከትሎ ለተመረጡ ወረዳ ቤተ ክህነት ሠራተኞች፣ ለአድባራት አስተዳዳሪዎችና የሰበካ ጉባኤ አባላት የግንዛቤና የትውውቅ መርሃግብር የተካሄደ ሲሆን በመርሃግብሩ የሀገረ ስብከቱ የክፍል ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
መርሃግብሩ በዘርፉ ባለሙያዎች ስለአስፈላጊነቱ እና ስለዝርዝር ጉዳዮች ገለጻ የተደረገ ሲሆን ሁሉም የኮሚቴው አባላት ራሳቸውን ለመርሃግብሩ ተሳታፊዎች አስተዋውቀዋል።
በተጨማሪም ከተሳታፊዎች ሃሳብ፣ አስተያየት እና ጥያቄ የቀረበ ሲሆን ለተነሱ ጥያቄዎች የኮሚቴው አባላት ምላሽ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም የሀገረ ስብከቱ መንፈሳዊ ትምህርትና የካህናት አገልግሎት ክፍል ኃላፊ መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ዮሐንስ ምሕረቱ በጸሎት ፈጽመዋል።
