ኤክቱስ ጥቅምት 08/2018 ዓ.ም

በ44ተኛው ዓለም አቀፍ ጠቅላላ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በከፍተኛ የሥራ አፈጻጸም ማለትም በመልካም አስተዳደር፣ ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት፣ ሰበካ ጉባኤን በማጠናከር፣ ሰንበት ትምህርት ቤትን በማደራጀት፣ ራስ አገዝ ልማትን በማስፋፋት፣ በገንዘብ ንብረትና አጠባበቅ፣ በቅርሳቅርስ ጥበቃ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትንና የተለያዩ ኅትመቶችን በማሰራጨት፣ በምግባረ ሠናይ ሥራ ባሳየው ከፍተኛ አፈጻጸም በምድብ 6 ከተካተቱት አህጉረ ስብከቶች መካከል አንደኛ በመውጣት የምስክር ወረቀትና የመቶ ሃምሳ ሲሲ ባለ ሁለት እግር የሞተር ሳይክል ተሸላሚ ሆነ።