በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ለአርባ ደቀ መዛሙርት ሥልጣነ ክህነት ሰጡ!

ኤክቱስ ታኅሣሥ 19/2018 ዓ.ም

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የታኅሣሥ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሚከበርበት በጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ለ33 ደቀ መዛሙርት የዲቁና ለ7 ዲያቆናት የቅስና በአጠቃላይ ለ40 ደቀመዛሙርት ሥልጣነ ክህነት ሰጥተዋል።

ደቀ መዛሙርቱ ለዲቁና እና ለቅስና የሚያበቃቸውን መንፈሳዊ ትምህርት ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆኑ ከመሾማቸው በፊትም ብቁ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ፈተና ተሰጥቷቸው ማለፋቸው ተገልጿል።

ብፁዕነታቸው በሰጡት አባታዊ ቃለ ምዕዳን ክህነት ትልቅ ኃላፊነት መሆኑን አሳስበው አዲሶቹ አገልጋዮች መንጋውን በንጽሕና፣ በትጋትና በቅንነት እንዲጠብቁ አደራ ብለዋል።

Scroll to Top