ኤክቱስ ሐምሌ 6/2018 ዓ.ም
በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በኮቾሬ፣ ገደብና ጮርሶ ወረዳዎች ቤተ ክህነት በጨለለቅቱ ከተማ ሲገነባ የቆየው የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ግንባታ ተጠናቆ በብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ተባረከ።
በመርሃግብሩ መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ዮሐንስ ምሕረቱ የሀገረ ስብከቱ የመንፈሳዊ ትምህርትና የካህናት አገልግሎት ክፍል ኃላፊ፣ የወረዳ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሰላም እኔምአየሁ ዓለሙ፣ የወረዳ ቤተ ክህነቱ ዋና ጸሐፊ በኩረ ትጉሃን አስቻለው ገብረ መድኅን፣ በኩረ ትጉሃን አእምሮ ሙሉ የሁለቱ አድባራት አስተዳዳሪ ፣ ካህናትና ዲያቆናት እንዲሁም በርካታ የአካባቢው ምዕመናን በሥነ ሥርዓቱ ላይ በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ ሆነዋል።
ይህ አዲስ የቤተ ክርስቲያን ሕንጻ መመረቅ በአካባቢው ያለውን የወንጌል አገልግሎት ይበልጥ ለማስፋፋት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተገልጿል።
