በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

በጉባኤው ማጠቃለያ ቀን 28 ምዕመናን የንሥሐ አባት እንዲይዙ ተደረገ!

ኤክቱስ ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም

በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል መመሪያ ሰጪነት በማታው (በመጨረሻው) የጉባኤ መርሃግብር ሃያ ስምንት ምዕመናን የንሥሐ አባት እንዲኖራቸው ተደርጓል።

ይህም እያንዳንዱን ምዕመን ሕይወታቸውን በቅዱሳት ምሥጢራት ተሳታፊ ሆነው እንዲመሩ ለማስቻል የተከናወነ የመንፈሳዊ አገልግሎት አካል ነው።

በዕለቱ በተላለፈው ትምህርት ምዕመናን በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲጸኑና እርስ በእርስ በፍቅር እንዲሁም በሰላም እንዲኖሩ ጥሪ ቀርቧል።

የንሥሐ አባት ለመያዝ የተመዘገቡ ምዕመናንም በአስቸኳይ አባት ተመድቦላቸው በመንፈሳዊ አባቶቻቸው እየተመሩ ጠንካራ መንፈሳዊ መሠረት እንዲኖራቸው ሊደረግ እንደሚገባ መመሪያ ተሰጥቷል።

Scroll to Top