ኤክቱስ ኅዳር 05/2019 ዓ.ም
በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል መሪነት ለአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ለሰበካ ጉባኤ አባላትና ለሚመለከታቸው አካላት በአብያተ ክርስቲያናት የአገልጋዮች የደመወዝ እርከን፣ ማስተካከያና ጭማሪ አፈጻጸም የግንዛቤ መስጫ ሰነድ ዙሪያ ሰፊ ውይይት በዲላ ከተማ መካሄዱን መዘገባችን ይታወሳል።
በተመሳሳይ መልኩ በብፁዕነታቸው መመሪያ ሰጪነት በሀገረ ስብከቱ ልዑካን አማካኝነት በይርጋጨፌ፣ በኮቾሬ፣ ገደብና ጮርሶ ወረዳ ቤተ ክህነት ለሚገኙ አድባራት አስተዳዳሪዎች እና የሰበካ ጉባኤ አባላት የደመወዝ እርከንና ማስተካከያ አፈጻጸም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል።
