በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

በብፁዕነታቸው መሪነት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ልዑካን በዲላ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ!

ኤክቱስ የካቲት 3/2018 ዓ.ም

​በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሲሰጥ የነበረው የሥልጠና መርሐ ግብር መጠናቀቁን ተከትሎ በብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ መሪነት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ልዑካን በዲላ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

​በጉብኝቱ ወቅት ልዑካኑ በደብሩ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙትን የዳቦ ቤት አገልግሎት፣ የቡና ተክል ልማት እንዲሁም የብርቱካን፣ የፓፓያ እና የንብ ማነብ ወዘተ… የግብርና ምርቶችን ተመልክተዋል።

እነዚህ የልማት ሥራዎች ደብሩ መንፈሳዊ አገልግሎቱን በራሱ አቅም ለመደገፍና ለአካባቢው ማኅበረሰብም የሥራ ዕድል ለመፍጠር እያደረገ ያለውን ጥረት የሚያሳዩ መሆናቸው ተገልጿል።

​ልዑካኑ ደብሩ ካለው መንፈሳዊ አገልግሎት ጎን ለጎን እንዲህ ያሉ የልማት ሥራዎች ላይ መሰማራቱ በሌሎች አህጉረ ስብከት ለሚገኙ አድባራትና ገዳማት አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። ይህም የቤተ ክርስቲያኒቱን የኢኮኖሚ አቅም ከማጠናከር ባሻገር የአካባቢውን የተፈጥሮ ሀብት ለመጠበቅ ያለውን ፋይዳ አድንቀዋል።

Scroll to Top