የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ተግባርና ኃላፊነት
ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሆኖ፡-
፩. በዋናነት በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ክልል ውስጥ ያለችውን ቤተክርስቲያን በበላይነት ይመራል ይጠብቃል፡፡
፪. በሀገረ ስብከት ውስጥ ለሚገኙ ካህናትና ምዕመናን መንፈሳዊ አባትና መሪ እንደመሆኑ መጠን ሃይማኖታቸውን ፣ሥርዓተ ቤተክርስቲያናቸውንና ኦርቶዶክሳዊ ትውፊታቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ ብርቱ ጥበቃ ያደርጋል ፣መመሪያና ቡራኬ ይሰጣል፡፡
፫. በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ ስድስትና ሰባት ፣በህገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 54 ተራ ቁጥር አራት በተደነገገው መሠረት በሥነ ምግባራቸው የተመሰገኑትንና በትምህርት ደረጃቸው ብቁ የሆኑትን ቀሳውስትና ዲያቆናት በመሾም በሀገረ ስብከቱ ለሌላው አርአያ የሚሆኑ ካህናት ማፈፍራት፡፡
፬. በሀገረ በስብከቱ ወሰን ውስጥ ማንኛውም መዋቅራዊ ደረጃውን ጠብቆና አጠናቆ የቀረበን የቤተክርስቲያን ጉዳይ በተመለከተ ከሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ ጋር በይግባኝ ተመልክቶ ተገቢውን ውሳኔ ይሰጣል እንደ ጉዳዩ ክብደት ለቅዱስ ሲኖዶስ አስተላልፎ የመጨረሻውን ውሳኔ እንዲያገኝ ያደርጋል፡፡ እንደ አስፈላጊነቱም ምህረትና ይቅርታ ያደርጋል፡፡
፭. በመንበረ ጵጵስናው ዋና ከተማ መርሐ ግብር በማውጣት እንደ ዕድሜአቸውና ዕውቀታቸው በመከፋፈል እንደ ሁኔታው ሰብስቦ ያስተምራል፡፡