የሀገረ ስብከቱ የገንዘብ ቤት ሥራና ኃላፊነት
፩.ገንዘብን በህጋዊ ደረሰኝ (ካርኒ) ይቀበላል፡፡
፪.ለማንኛውም የገንዘብ ወጪ ህጋዊ ትዕዛዝ ሲደርሰው ብቻ ክፍያ ይፈጽማል፡፡
፫.ገቢና ወጪውን በተለየ በተዘጋጀ የገቢና የወጪ መዛግብት ላይ ይመዘግባል እንዲሁም ሂሳቡን በጥንቃቄ መዝግቦ ይይዛል፡፡
፬.በየወሩ መጨረሻ በጠቅላላ የገባውና የወጣውን ገንዘብ ልክ ከወጪ ቀሪውን ከሂሳብ ክፍሉ መዛግባት ጋር ያመሳክራል፡፡