የሀገረ ስብከቱ የቁጥጥር ክፍል ሥራና ኀላፊነት
፩.ልዩ ልዩ ገቢና ወጪ የተደረገባቸውን ካርኒዎችና ሰነዶች ህጋዊ መሆናቸውን ይመረምራል እንዲሁም ገንዘቡ በትክክል ተቆጥሮ በባንክ መቀመጡን ያረጋግጣል ፡፡
፪.የሒሳቡ አያያዝ አጠባበቅ ትክክል መሆኑንና አለመሆኑን በዝርዝር መዝግቦ በየሦስት ወር ለአስተዳደር ጉባኤ ሪፖርት ያቀርባል፡፡
፫. ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር የሀገረ ስብከቱን ንብረት በየዓመቱ ኦዲት ያደርጋል፡፡
፬. በሀገረ ስብከቱ ለዓመት ከተመደበው በጀት በላይ ወጪ እንዳይሆን ይቆጣጠራል፡፡