በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል ሥራና ኀላፊነት

፩. የእግዚአብሔርን ወንጌለ መንግስት መስበክና ትምህርቱንም ማስፋፋት

፪. ምዕመናን በሚረዱት እና በሚያውቁት ቋንቋ ትምህርተ ወንጌል እንዲሰጥ ተከታዮች እንዲበዙና በሰበካ ጉባኤም እንዲመዘገቡ  በማድረግ ሐዋርያዊ ተልእኮውን ይፈጽማል

፫. የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በቅዳሴ ዕለት በክብረ በዓላት በመንፈሳዊ ጉባኤያት በሀዘንና በደስታ ስፍራዎች እንዲሰጥ ያደርጋል ተፈጻሚነቱን ይከታተላል

፬. ያለ ፈቃድ እንሰብካለን እናስተምራለን የሚሉ ግለሰቦችን መቆጣጠር ወደ ህጋዊ መስመር እንዲመጡ ማድረግ

፭. በሀገረ ስብከቱ የሚገኙ ሰባኪያነ ወንጌልን ማብቃት ማሰልጠን ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ እና  በበጎ ፈቃድ የሚያገለግሉ ሰባኪያነ ወንጌልን ማስልጠን ህጋዊ ፈቃድ እንዲያገኙ ማድረግና መከታተል

፮.የስብከት ኬላዎችን በማቋቋም የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ምዕመናን በሚሰሙት ቋንቋ እንዲሰበክ ያደርጋል፡፡

፯. ለምዕመናን፣ለሰንበት ት/ቤት አባላትና ለካህናት ምቹ ሁኔታዎችን በማመቻቸት የትምህርተ ሃይማኖት ኮርሶችን ይሰጣል እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡

፰. ከቤተክርስቲያን እውቅና ውጪ የሆኑ የህትመት የድምጽና የምስል ውጤቶችን  እንዳይሰራጩ  ይቆጣጠራል  ተፈጻሚነቱን  ይከታተላል፡፡ እንዲሁም የተፈቀደላቸው  ለምዕመናን እንዲሰራጩ ያደርጋል፡፡

Scroll to Top
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት