የሀገረ ስብከቱ የመንፈሳዊ ትምህርት ክፍል ሥራና ኀላፊነት
፩.በሀገረ ስብከቱ በሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መንፈሳዊና ዘመናዊ ት/ቤት እንዲቋቋም ያደርጋል እንዲሁም ለተማሪዎችም የሚያስፈልገውን በጀት እንዲመደብ የሚመለከታቸውን ሁሉ ያስተባብራል፡፡
፪.የትምህርት መስጫ ቦታዎች አመቺ እንዲሆኑና መምህራን ጉባኤያቸውን ሳይፈቱ እንዲያስተምሩ ያደርጋል፡፡
፫. ቤተ መጻሕፍት እንዲያቋቁሙና ካህናት ዲያቆናት የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ተገኝተው እንዲያነቡ አስፈላጊው ሁሉ እንዲፈጸም ያደርጋል፡፡
፬. ህጻናት በሥነ ምግባርና በሃይማኖት ተኮትኩተው እንዲያድጉ ያደርጋል፡፡ ፭. የመማር የማስተማር ሂደት በተሳለጠ መልኩ በቅርበት ሆኖ ይቆጣጠራል፡፡