የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ ሥልጣንና ተግባር
፩. የሀገረ ስብከቱን ጠቅላላ የጽህፈት ፣የሂሳብና የንብረት አጠባበቅ ሥራዎችን እንደዚሁም የልዩ ልዩ ክፍሎችን የሥራ ሂደት በቅርቡ እየተከታተለ በመቆጣጠር ይሠራል ያሠራል፡፡
፪. የወረዳ ቤተክህነቶች ለሀገረ ስብከቱ ገቢ የሚያደርጉትን ክፍያ በወቅቱ ገቢ መሆኑን ይከታተላል፡፡
፫. በሀገረ ስብከት ውስጥ የሚገኙ የምዕመናን አኃዛዊ መረጃዎች እንዲያዙ ያደርጋል፡፡
፬. የሀገረ ስብከቱን የሥራ አፈጻጸምና የሒሳብ ይዘት መግለጫ ለመጭው ዓመት ከሚፈቅደው ዓመታዊ የገንዘብ ድልድል (በጀት) ጋር አዘጋጅቶ በሥራ አስኪያጁ አማካኝነት ለአስተዳደር ጉባኤ ያቀርባል፡፡
፭.የሀገረ ስብከቱን የልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች የሚቀርብለትን የሥራ ክንውን እንዲሁም አኃዛዊ መረጃዎችን በማጠቃለል በየሦስት ወሩ ለአስተዳዳር ጉባኤ ሪፖርት ያቀርባል፡፡