በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር

፩. የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ተጠሪነቱ ለሊቀ ጳጳሱ ይሆናል

፪. ከበላይ የሚመጡ ውሳኔዎች፣መመሪያዎችን እና የሀገረ ስብከቱ የአስተዳደር ጉባኤ ውሳኔዎችን በየደረጃው ለሚገኙት ለበታች ላሉ መዋቅሮች በወቅቱ እንዲደርሱ ያደርጋል አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡ ጥፋት ሲፈጸምም ከሊቀጳጳሱ መመሪያ እየተቀበለ እንደጥፋቱ መጠን የቃልና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፡፡

፫. የሀገረ ስብከቱን አኃዛዊ መረጃዎች/ስታትስቲክስ/ የበጀት ዓመቱን የሥራ ክንውን እና የፋይናንስ ሪፖርት ለመንበረ ጵጵስናው ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ በወቅቱ ያቀርባል፡፡

Scroll to Top
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት