በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ሀገረ ስብከቱ የሚያከናውናቸው ተግባራት

የሀገረ ስብከቱን ዓላማ  ከግብ ለማድረስ በቀጣዩ አሥር ዓመት ሀገረ ስብከታችን የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፡፡

፩. የሀገረ ስብከቱን ሙሉ ስታስቲካዊ መረጃዎችን አስባስቦና  አጠናቅሮ ይይዛል

፪.ስብከተ ወንጌል በሁሉም የሀገረ ስብከቱ ወሰን እንዲስፋፋ ያደርጋል፡፡

፫. ሁለ ገብ የአብነት  ት/ቤቶችን በቅደም ተከተል ያቋቁማል ያደራጅማል

፬. በሀገረ ስብከቱ ክልል ውስጥ ያሉት ገጠር አብያተክርስቲያናት በተለያየ ምክንያት የተዘጉ እንዲከፈቱ አገልጋይ እጥረት ያለባቸው እንዲሟላላቸው ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል፡፡

፭. አድባራቱን በመንፈሳዊና በማህበራዊ ተግባር እንዲተባበሩ ያደርጋል፡፡

፮.የሰንበት ት/ቤት ባልተቋቋመባቸው አብያተ ከርስቲያናት የማቋቋም ሥራ ይሰራል በተቋቋመበትም ቦታ የማጠናከር ሥራ በትጋት ይሰራል፡፡

፯.በሀገረ ስብከታችን በሚነገሩ ሦስት ቋንቋዎች ማለትም በጌዴኡፋ፣ኮሬቲና ቡርጂ ቋንቋዎች  የትርጉም ሥራ ፣መንፈሳዊ መጻህፍትን ፣መዝሙራትንና ወዘተ የመተርጎም  ሥራ ይሰራል፡፡

፷.በሀገረ ስብከቱ ወሰን ውስጥ ያሉት አብያተክርስቲያናት በሀብትና ንብረት ራሳቸውን እንዲችሉ በኢኮኖሚ  ያስተሳስራል፡፡

፱.ሁሉም በሀገረ ስብከቱ ያሉ አብያተክርስቲያናት ይዞታ ማረጋገጫ እንዲኖራቸው ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል፡፡

፲. የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን በመዘርጋትና በማዘመን ለውጥ ለማምጣት ይሠራል፡፡

፲፩. በሀገረ ስብከታችን ከሀያና ከዚያ ዓመት በላይ ቤተክርስቲያን አገልግለው ሥጋዊ  አቅማቸው የደከመ ካህናት  በጡረታ ከማግለል ይልቅ እስከ እረፍተ ዘመናቸው በጸሎት እንዲያገለግሉ በእንክበብካቤ እንዲያዙ ይሰራል ፣በጣም አቅመ ደካማ ሆነው የሚረዳቸው ቤተሰብ ሳይኖራቸው ሲቀር ቤተክርስቲያን ልዩ የእንክብካቤ ማዕከል (Rest Home) በማዘጋጀት እስከ ዓረፍተ ዘመናቸው ድረስ በእንክብካቤ እንዲያዙ ለማድረግ ጥረት ያደርጋል፡፡

፲፪.የቀብር ቦታዎችን በዘመናዊ መልኩ በማደራጀት በጽዳትና በክብር እንዲያዙ ያደርጋል፡፡

Scroll to Top
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት