በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ሀገረ ስብከቱ ለኮቾሬ ገደብና ጮርሶ ወረዳዎች ቤተ ክህነት የሞተር ሳይክል ስጦታ አበረከተ!

ኤክቱስ የካቲት 16/2018 ዓ.ም

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጥቅምት 08/2018 ዓ.ም በ44ተኛው ዓለም አቀፍ ጠቅላላ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ባሳየው ከፍተኛ አፈጻጸም በምድብ 6 ከተካተቱት አህጉረ ስብከቶች መካከል አንደኛ በመውጣት የምስክር ወረቀትና የመቶ ሃምሳ ሲሲ ባለ ሁለት እግር የሞተር ሳይክል መሸለሙ ይታወቃል።

ይህንን ሞተር ሳይክል በዛሬው ዕለት ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ለወረዳ ቤተ ክህነቱ ዋና ጸሐፊ ለበኩረ ትጉሃን ቀሲስ አስቻለሁ ገብረ መድኅን ያስረከቡ ሲሆን የበለጠ ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት እና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ለማከናወን እንደሚያግዛቸው ገልጸዋል።

1 thought on “ሀገረ ስብከቱ ለኮቾሬ ገደብና ጮርሶ ወረዳዎች ቤተ ክህነት የሞተር ሳይክል ስጦታ አበረከተ!”

  1. Pingback: ursodiol medication

Comments are closed.

Scroll to Top