ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጅ ሀገረ ስብከት ጳጳስ በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፍ ተሰማርተው በአዲስ አበባ ከሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ጋር በሀገረ ስብከቱ በሚከናወኑ ዕቅዶች ዙሪያ ውይይት አደረጉ።
ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ በሀገረ ስብከቱ እየተከናወኑና ወደፊት ሊተገበሩ በታቀዱ ዕቅዶች ዙሪያ በአዲስአበባ ከተማ ከሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ጋር በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የነገረ መለኮት መማሪያ ክፍል የጋራ ውይይትና ምክክር አደረጉ። ለምክክሩ መነሻ የሚሆን ሰነድ የቀረበ ሲሆን በሰነዱ በሀገረ ስብከቱ ታሪካዊ ጉዞ፣ አሁናዊ ሀገረ ስብከቱ ያለበት ነባራዊ እውነታና ተግዳሮት፣ ወደፊት በሀገረ ስብከቱና በምእመናን […]